«በታላቁ አንዋር መስጂድ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት የኃይል እርምጃ ሰላት ለመስገድ በሄዱ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ።» የዓይን እምኞች

ስማቸውን እንዳንጠቅስ ድምፃቸውንም እንዳናሰማ የጠየቁ አንድ የዐይን እማኝ በመስጊዱ ዙሪያ ተከስቶ የነበረውን ሁኔታ ሲገልፁ «ከፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ የወደቀ ሰው አይቻለሁ፣ ሁኔታውም አስፈሪ ነበር»ብለዋል።ጉዳት መድረሱን እና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የሚያሳዩ ልዩ ልዩ ምስሎችም በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሲዘዋወሩ ታይቷል።…