የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን በትግራይ ምርጫ ‘በአስቸኳይ’ እንዲካሄድ ጠየቁ

የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በትግራይ ክልል ምርጫ ‘በአስቸኳይ’ እንዲካሄድ ጠየቁ። በፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት መሠረት በትግራይ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ክልሉን መምራት የሚችለው ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት መሆኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገልጸዋል። “ራስን በራስ ማስተዳደርን መሠረት በማድረግ በአስቸኳይ ወደ ምርጫ መሄድ አለብን” ብለዋል የህወሓ…