ሰው ሲሞት በዘፈን እና በጭፈራ የሚሸኘው የደቡብ ኢትዮጵያው ማኅበረሰብ

ሞት በሁሉም ዘንድ ሁሌም አዲስ ነው። በመጣ ቁጥር የሚያስደነግጥ በብዙ ማኅበረሰቦች ዘንድም ማቅ የሚያስለብስ እና እንባ የሚያራጭ ክስተት ነው። ሟችን ለመሰናበትም ሆነ ቤተሰቡን ለማጽናናት የሚሰበሰበውም ሐዘኑን የሚገልጸው እንባውን እያፈሰሰ፣ ደረቱን እየደቃ ነው። በአንዳንድ አካባቢ ዘመድ የሞተባቸው ቤተሰቦች ጥቁር መልበስ፣ ፀጉር መላጨት እና ወትሮ ሲፈጽሙት ከነበሩ የደስታ ድርጊቶች መታቀብ የተለ…