ኢትዮጵያ የገባችበት የውጭ ዕዳ ጫና አጣብቂኝና የአበዳሪ አገሮች ፖለቲካዊ ፍልሚያ

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ በአሜሪካ መካሄድ የጀመረውን የዓለም ባንክና የአይኤምኤፍ የጋራ ጉባዔ መጀመር አስመልክቶ፣ ባለፈው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች ያለባቸውን ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ማቅለያና የመክፈያ ጊዜን በመልሶ ማዋቀር ለማራዘም ያቀረቡት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ጥያቄ መዘግየት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። በተለይ ኢትዮጵያ፣ ጋናና ዛምቢያ የገጠማቸው የዕዳ ጫና ቀውስ እየሰፋ በመሄዱ፣ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ዕዳቸውን ለማቅለልና የመክፈያ ጊዜው እንዲራዘም ያቀረቡት ጥያቄ ላይ በአስቸኳይ መወሰን ያስፈልጋል ብለዋል። ‹‹ሁሉም አበዳሪ ወገኖች ቃላትን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት ጊዜው አሁን ነው፤›› ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ የአገሮቹን በተለይም የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ መልሶ በማዋቀር የዕፎይታ ጊዜ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አገሮቹ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከቻይና መንግሥት የወሰዱት ብድርና የብድር ስምምነቱ ሚስጥራዊ መሆን፣ ሌሎች አበዳሪ አገሮች የቀረበላቸውን የዕዳ መልሶ የማዋቀር ጥያቄ ለመመለስ መቸገር ነው፡፡ አሜሪካ በዓለም የገንዘብ ድርጅት ላይ ያላትን ተፅዕኖ በመጠቀምና የቡድን 20 አገሮችን በማስተባበር፣ ታዳጊ አገሮች ከቻይና ያገኙት የውጭ ብድር ግልጽ ካልሆነ የዕዳ ጫናውን የማቃለል ተግባር እንዳይፈጸም ጫና እያደረገች ነው። ለዝርዝር ዘገባው ሊንኩን ይጫኑ ። https://www.ethiopianreporter.com/117779/