አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ አገር ያዳነ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት በህዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም!

አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ አገር ያዳነ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት በህዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም!
1) ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ያደረገው መንግስት ነው። አቶ ሬድዋን ሁሴን “ህወሓት ስጋት አለበት” ብሏል። ለትህነግ ደህንነት ብለው ነው ያን ወንጀለኛ ታጣቂው እንዳይፈታ ያደረጉት እንደማለት ነው። ነገር ግን ሱዳን ያለውም እንዳይፈታ ተደርጓል። ሱዳን የትግራይ አካል አይደለም። ሱዳን ስጋት ስላለበት አይደለም የሱዳኑ ኃይል ትጥቅ ያልፈታው። አላማው ህዝብን ለማስጠቃት ዝግጅት ነው።
2)ጌታቸው ረዳ ለቅሶ ቤት ተገኝቶ ወልቃይትን በኃይል እንይዛለን ማለቱ ተዘግበ፣ል። ከአውሮፓና አሜሪካ ሄደው ሰሞኑን ሱዳን ያለው የትህነግ ኃይል ጋር ስብሰባ ያደረጉ የትህነግ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወልቃይትን በኃይል አስመልሳለሁ እንዳላቸው በመግለፅ “እንዘጋጅ” የሚል ቅስቀሳ አድርገዋል።
በሌላ ስብሰባ ትህነግ ለምን ትጥቅ እንደማይፈታ የተጠየቀው ጌታቸው ረዳ “ከእኛ ውጭ ሆነው ለጦርነት የሚዘጋጁ ኃይሎች አሉ።” ብሏል። ኃላፊነት ላለመውሰድ ነው። የትህነግን ኃይል ለጦርነት የሚያዘጋጁት እነ ጌታቸው ጋር የሚውሉት ጀኔራሎች ናቸው። ዋናው ግን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ አምኗል።
3) እነ አዲሱ አረጋ የዘር ፍጅት አውጀዋል። ይህን የዘር ፍጅት የሚፈፅሙት ደግሞ በኦነግ ሸኔ እና ኦነግ ሸኔ አስመስለው በሚያሰማሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አዲስ ምልምል እያሰለጠነ ነው። ኦነግ ሸኔም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ ሳይፈቱ ሌሎቹ እንዲፈቱ ማድረግ የዘር ፍጅቱን ለማስፈፀም ነው የሚሆነው።
4) በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትግራይን ይይዛል የተባለው መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ አዋሳኞች ወጥቷል። በዚህ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ በትህነግ የዘር ፍጅት ሲፈፀምበት የኖረና አሁንም እድል ቢያገኝ ሊበቀለው የሚፈልገው ነው። በዚህ ሁኔታ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት ህዝብን ለዘር ፍጅት ማመቻቸት ነው።
5) በተለያዩ ጊዜያት ህዝብ ላይ ጥቃት ሲፈፀም መከላከያ አያገባውም፣ ትዕዛዝ አልተሰጠውም፣ በክልሎች ጉዳይ አይገባም እየተባለ የሚደርሰው ልዩ ኃይል ነው። ይህ ሴራ ባልተቀየረበት ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ ማድረግ ህዝብን ለአሸባሪዎች አሳልፎ መስጠት ነው።
አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት ህዝብን ለማስጠቃት የተሸረበ ሴራ ነው። የልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በተመለከተ በተደረጉት ስብሰባዎች መጀመርያ አሸባሪን ትጥቅ አስፈቱ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቀርቧል። አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ፣ የህዝብ ደህንነት ሳይረጋገጥ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት በህዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት እንደማወጅ ነው።
መከላከያ ሰራዊትን ደጋግሞ የመታው የትህነግ ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ፣ ህዝብን እየጨፈጨፈ የሚገኘው ኦነግ ሸኔና ኦነግ ሸኔን መስሎ የሚጨፈጭፈው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ የዘር ፍጅት ስጋት ያለበት ህዝብ ዋስትና የሆነ ኃይል ትጥቅ ይፍታ የሚል በህዝብ ላይ የታወጀን ጦርነት ማስቆም ግዴታ ነው። ቅድመ ሁኔታ እንኳን ሳያሟሉ፣ ለትህነግ እየተቆረቆሩ ልዩ ኃይልን ለማስፈታት ሲሞክር አይሆንም ማለት ያስፈልጋል።
በዚህ ሁኔታ ልዩ ኃይሉ ትጥቅ እንዲፈታ ውሳኔ የወሰኑ አካላት ህዝብን ለማስመታት የተባበሩ እንደሆኑ መታወቅ አለበት።