የዜጎች ደሕንነትና የሃገር ሰላም በእጁ ያሉት የደሕንነት ተቋም ሽባ ሆኗል፤ ተመስገን ጡረታ ወጥቶ ምክትሉ አቶ ታዜር ቢተካስ ?

ተመስገን ጡረታ ወጥቶ ምክትሉ አቶ ታዜር ቢተካስ ? ሲሳይ ቶላ የሽብር ኔትወርክ አጣማጅ ስለሆነ ወደ ሌላ ቢዛወርስ ?

የደህንነት ተቋሙን በተመለከተ በደምላሽ ገብረሚካኤል እና በመሃመድ አደም ጊዜ በተደጋጋሚ ተናግረናል። ( * ዝርዝር ሊንኮችን ከታች አስቀምጫለሁ * ) ዛሬም ይህ አሳሳቢ ሽባ እየሆነ ስላለ ተቋም እንጩኽ ! የሃገር ሰላምና የዜጎች ደሕንነት በእጁ ያለ ተቋም ነው ።

በተመስገን ጥሩነህ የሚመራው የደሕንነት ተቋም ለሃገርም ለሕዝብም የማይጠቅም ነው። ተቋሙን ማን እየገደለው ነው ? የተመስገን ስራ መልቀቂያ ተቀባይነት አግኝቶ በምትኩ አቶ ታዜር ገብረእግዚአብሄር ቢሾምስ ? መንግስት የደሕንነት ተቋሙን ጉዳይ በቸልታ መመልከት የለበትም ፤ የሃገሪቱ ሰላም ማጣትና ሌብነት እንዲሁም የዜጎች ደህንነት ጉዳይ በዋናነት ያለው በደሕንነት ተቋሙ እጅ ላይ ነው ።

መንግስት የደሕንነት ተቋሙን እየገደለው ነው፤ መንግስት በባለስልጣናት የጋንጊስተሮች ቡድን እየተለፈ እየጣለው ነው ብለን ጮኸናል። ሰሚ ያልተገኘለት የደሕንነት ተቋሙ ወደ ሞት መፍጠን ይብስኑ በገዛ ተቋሙ ባለስልጣናት መሪነት የሚፈጸሙ ወንጀሎች እየበረከቱ መሄድ መንግስትን ያሳሰበው አይመስልም።

የአብይ አስተዳደር ወደ ስልታን ከመጣ ጀምሮ የደሕንነት ተቋሙ እንዲጠናከር ብንወተውትም በዘር የተቧደኑ ተረኛ ባለስልጣናት የራሳቸውን ኔትወርክ በመዘርጋት እና ደሕንነት ተቋሙ ውስጥ ካሉ ተሿሚዎች ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሃገርን አደጋ ላይ የሚጥል ወንጀል እየሰሩ መሆኑን እያየን እየታዘን ነው። የደህንነት ተቋም ኝባር ቀደም የሃገርን ደሕንነት እና ሰላም ማረጋገጥ የሚገባው ትልቅ ተቋም መሆኑ እየታወቀ በግጭት ጠማቂነትና በዘረፋ ላይ ባለስልታናቱ መሳተፋቸው ለሃገር ሕልውና ትልቅ ጋሬጣ ሆኗል።

ከለውጡ በኃላ በተለያየ ጊዜ የደሕንነት ተቋሙ ዝርክርክ አሰራርና አለመናነብን ጨምሮ የመረጃው ብተና ለአዳጋ እንዳያጋልጠን በመስጋት ጮኸናል።….

– የደሕንነት ተቋሙ ድክመት አግጥጦ እያየነው ነው።
https://www.facebook.com/photo.php?fbid=2529308467340341&set=pb.100007836377373.-2207520000..&type=3

– የደሕንነት ተቋሙ ኋላፊነትና ተጠያቂነት ከምን ድረስ ነው ???
https://www.facebook.com/photo.php?fbid=2487050501566138&set=pb.100007836377373.-2207520000..&type=3

– የጥቃት ኦፕሬሽን ሲፈፀም የደሕንነት ተቋሙ ምን ሲሰራ ነበር ?
https://www.facebook.com/photo.php?fbid=2371932923077897&set=pb.100007836377373.-2207520000..&type=3

– ይታሰብበት !!! የደሕንነት ተቋሙ ሊፈተሽ ይገባል።
https://www.facebook.com/photo.php?fbid=2361506570787199&set=pb.100007836377373.-2207520000..&type=3 

የደሕንነት ቢሮው የማሕበራዊ ድረገፆች የወሬ ማጣፈጫ የሚሆነው እስከመቼ ነው ? …… የደሕንነት ተቋሙ ሊፈተሽ ይገባል።
 
የደሕንነት ተቋሙ የማሕበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶችን ማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ውስጡን ሊያጠራ ይገባል።
የደሕንነት ተቋሙ ሞቷል !? — ከሞተ ንገሩን።

የተቋሙ ዝርክርክነት የተለያዩ አደጋዎችን እንድናስተናግድና እያስተናገድን እንድንቀጥል አድርጎናል እያደረገንም ነው። ከሌሎች አገራት የሚወሰደውን ልምድ ጨምሮ የሕግ የበላይነትን ተጠቅሞ የተቋሙን ዝርክርክነት ለማስተካከል ምንም መፍትሔ ሲወሰድ አላየንም።

የደሕንነት ተቋሙ የተንዛዛ አሰራር ሃገሪቷን ለችግር አቀባብሎ እንዳይሰጣት ያስፈራል። ጠንካራ የደሕንነት ተቋም ለአንድ አገር ሰላምና መረጋጋት ትልቅ መሰረት አለው። የደሕንነት ተቋሙ ሊፈተሽ ይገባል። ከብዙ ፈርጅ ችግሮች በተጨማሪ አሁን ያለበት መስመር ሃገሪቷን ለውስጥና ለውጪ ጠላት አሳልፎ ከመሸጥ ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም። በአፋጣኝ ይታሰብበት። #MinilikSalsawi