ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በጠና ታመዋል! ጀነራሉ በአሁኑ ሰዓት መንቀሳቀስ አይችሉም!

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በጠና ታመዋል!
ጀነራሉ በአሁኑ ሰዓት መንቀሳቀስ አይችሉም!
Imageህክምናቸውን በውጪ ሀገር መከታተል እንዳለባቸው ከዶክተራቸው ቢነገራቸውም ከወራት በፊት ወደ ውጪ ሒደው ለመታከም ቢሞክሩም የአብይ አህመድ አገዛዝ ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ከቦሌ አየር ማረፊያ አውሮፕላን እንዲመለሱ ተደርገዋል።
የብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወይዘሮ መነን ሀይለ እንደገለፀችው ጀነራሉ በተለይ ትላንት እና ዛሬ ክፉኛ መታመማቸውን እና መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።
በጠና መታመማቸውን ተከትሎ ዶክተራቸው ማስታገሻ ቢሰጧቸውም እንደጠናባቸው ወይዘሮ መነን ገልፀዋል። ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል ያሉት ወይዘሮ መነን ለሀገራቸው ታላቅ ውለታ የዋሉን ሰው ህክምና መከልከል እጅግ ያማል ብለዋል።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ የአማራ ህዝብ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ወደ ውጪ ሒደው ህክምና እንዲያደርጉ ጫና ማድረግ አለባቸው።
ለጀነራሉ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ የህክምና ወጪዎችንም በመተባበር እና በመተጋገዝ የጀነራል ተፈራ ማሞን ህይወት እንድንታደግ ጥሪ ቀርቧል።