አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾማቸው ተገለጸ

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከዚህ በፊት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት እንዲሁም በመንግሥት እና በህወሓት መካከል ፕሪቶሪያ ላይ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ነው ጊዜያዊ መንግሥቱ የሚቋቋመው።…