ከሶማሊላንድ ወደ ኢትዮጵያ ለተሰደዱ 100ሺ ለሚጠጉ ስደተኞች 41.7 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

ባለፈው አራት ሳምንታት ውስጥ 100,000 የሚጠጉ ስደተኞች በሶማሊላንድ ሶል ግዛት ላስኖድ በነበረው አለመረጋጋት ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መፍለሳቸውን ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

እንደ UNHCR መረጃ ስደተኞቹ የተሰደዱበት ዳዋ ዞን የአጠቃላይ የህዝብ ብዛቱ 497,00 ተብሎ የሚገመት ሲሆን ከዚህ ቀደም ስደተኞችን ተቀብሎ አያውቅም። በዚህም በዞኑ የተቋቋሙ የስደተኛ ካምፖች/ቦታዎች የሉም ነው የተባለው።

ታዲያ እነዚህን ስደተኞች ለማስተናገድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (RRS)፣ UNHCR፣ ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎችና ግብረሰናይ ድርጅቶች የአደጋ ጊዜ ምላሽ እቅድ አዘጋጅተው ይፋ አድርገዋል።

በዚህ እቅድ ላይ እንደተጠቀሰው ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ስደተኞች አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት ወደ 41.7 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የምግብ፣ የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት፣ የመጠለያ፣ የመሠረታዊ እቃዎች እና የጤና፣ የስነ-ምግብ እና የጥበቃ አገልግሎቶች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክቷል።

በተሰራ ፈጣን ቅኝት ስደተኞቹ የምግብ፣ የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት፣ የመጠለያ፣ የመሠረታዊ እቃዎች እና የጤና እና የጥበቃ አገልግሎቶች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክቷል።

በሶማሌ ክልል የሚገኘው ዶሎ ዞን በድርቅ ከተጎዱ አከባቢዎች አንዱ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን የቁም እንሰሳቸውን ያጡበትና ለችግር የተጋለጡበት አከባቢ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በድርቁ ምክንያት የተከሰቱ በሽታዎች ነዋሪውን ጎድተውታል። በአከባቢው በድርቅና በጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ከ44,586 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም የሚገኙበት ነው።