ብሪታንያ የጀልባ ስደተኞች እንዳይመጡባት ያወጣችው እቅድና ትችቱ

ብሪታንያ ያረቀቀችው አዲስ ሕግ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ከብሪታንያ አባሮ ወደ ሩዋንዳ ወይም ወደ ሌላ ደኅንነቱ የተጠበቀ ሦስተኛ ሀገር እንዲላኩ የሚያደርግ ነው።ብሪታንያ በተለይ በጀልባ የሚመጡ ስደተኞችን አስገድዳ ከሀገርዋ ለማባረር የምታደርገው ዝግጅት በስደተኞችና በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በእጅጉ መተቸቱ ቀጥሏል።…