የመንግሥታቱ ድርጅት ቀይ ባሕር ላይ የተደቀነ አደጋን ለማስወገድ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ገዛ

የተባበሩት መንግሥታት የመን ባሕር ዳርቻ አካባቢ በአንዲት አሮጌ መርከብ ምክንያት በተፈጥሮ ላይ የተጋረጠን አደጋ ለመቀልበስ በሚል ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ገዛ። አደጋውን ታስከትላለች የተባለችው መርከብ እየበሰበሰ ባለ መጫኛዋ ከአንድ ሚሊዮን በርሜላ በላይ ድፍድፍ ነዳጅ ጭና ቀይ ባሕር ላይ ለዓመታት ቆይታለች።…