የደቡብ ክልል ምክር ቤት እንደራሴዎች እሥር

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ አምስት የደቡብ ክልል ምክር ቤት እንደራሴዎችን ጨምሮ አለአግባብ ታሥረውብኛል ያላቸውን ስድስት የፓርቲውን አባላት መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው እንዳለው በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ ስድስት አባላቱ ከህገ ውጪ ከታሠሩ ከሳምንት በላይ ቢሆናቸውም እስከአሁን ግን ፍርድ ቤት አልቀረቡም።…