አዲስ አበባ ሸገር ሲቲ ተብሎ በተሰየመው በተለምዶ ሃያ ሁለት ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቤቶች ፈረሳ እንደቀጠለነው ተባለ።

[addtoany]

ዛሬ የካቲት 29/2015 ዓ/ም ከማለዳው ጀምሮ በተካሄደው የቤቶች ፈረሳ ከ400 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የአሻራ ምጮች ገልፀዋል።

የአማራ ተወላጆችን መሰረት ያደረገው የቤቶች ፈረሳ አሁን አሁን የጉራጌ ተወላጆችንም ማካተቱን የአሻራ ምንጮች አረጋግጠዋል።

በአንድ ሳምንት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተዎላጆችን ቤት አልባ እያደረገ የሚገኘው የኦሮሙማው አገዛዝ አሁንም ድረስ ይህንኑ ግፍና በደል አጠናክሮ መቀጠሉን ምንጮች ተናግረዋል።

የካቲት 28/2015 ዓ/ም ከ400 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ቀለም የቀባው አፍራሽ ግብረሃይሉ ዛሬ የካቴት 29/2015 ዓ/ም ከማለዳው ጀምሮ ከ400 በላይ ቤቶችን ማፍረሱን ምንጮች አረጋግጠዋል።

በዚህም የተነሳ በዛሬው ዕለት ብቻ በርካታ አባወራዎች እና እማ ዎራዎች ከነልጆቻቸው ጎዳናላይ መውደቃቸው ታውቋል።

አሻራ ሚዲያ