የ127ኛው የአድዋ ድል አከባበር በአዲስ አበባ

127 ኛው የአድዋ ድል ክብረ በዓል በብሔራዊ ደረጃ «አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት» በሚሉ መሪ ሀሳቦች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሯል። ሆኖም በበዓሉ አክባሪዎች እና በሥነ ሥርዓት አስከባሪ ፖሊሶች መካከል ፍጥጫ መፈጠሩ ተሰምቷል። ፖሊሶችም የበዓሉን ታዳሚ ለመበተን አስለቃሽ ጢስ ሲተኩሱና ድብደባ ሲፈጽሙ ታይተዋል።…