የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች በኪረሙ ወረዳ ተጠልለው በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ! ፣
ልዩ ኃይሉን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች በምስራቅ ወለጋ ጊዳ ኪረሙ ወረዳ ሃሮ አዲስ አለም ቀበሌ ተጠልለው በሚገኙ ከ60ሺ በላይ ተፈናቃዮች ላይ ዛሬ ታህሳስ 14/2015 ዓ/ም ከማለዳው ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸውን በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።
የክልሉ ልዩ ኃይል እና የወረዳው ፖሊሶች በአንድ ላይ ተቀናጅተው ድሽቃ በተባለ የቡድን መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ዛሬ ታህሳስ 14/2015 ዓ/ም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአራት አቅጣጫ ተኩስ እንደከፈቱባቸው የገለፁት የአይን እማኞቹ፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ በአስቸኳይ አከባቢው ተሰማርቶ እንዲታደጋቸው ተማፅኖ አቅርበዋል።
በኪረሙ ወረዳ ህዳር 9 እና ህዳር 20 /2015 ዓ/ም የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ እስር ቤት እንዳሉ በጅምላ የተረሸኑትን 81 እስረኞችን ጨምሮ ከ150 በላይ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን የአማራ ድምፅ መዘገቡ አይዘነጋም።
መረጃው የአማራ ድምፅ ነው