ከዚህ በፊት በለሚኩራ ክ/ከተማ ቁሊቲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመጀመሪያ ዙር 109ቤቶችች ሲፈርሱ ፤ በሁለተኛው ዙር ደግሞ 39 ቤቶች ፈርሰዋል።ይህ ሁሉ ሲደረግ ምንም አይነት የህግ አግባብ አልተከተሉም ። የቦታ ካሳ ዎይም ደግሞ ትክ አልተሰጣቸውም። በመሆኑም ቤት የፈረሰባቸው አባውራዎች እና እማውራወች ሜዳ ላይ ወድቀዋል ብለዋል።
አሁን ደግሞ ይህ አፍራሽ ግብረሃል የቀሩትን ቤችች ለማፍረስ እንቅስቃሴ ላይ ነው። ህዳር 26/2015 ዓ/ም ምንም አይነት የህግ አግባብ ባልተከተለ መልኩ አፍርሱ የሚል መልክት አስተላልፏል። እንዴት ቤታችንን አፍርሱ ትሉናላችሁ ። ቤታችንን አፍርሰን እንዴት ሜዳላይ እንወድቃለን ብለው የጠየቁትን በማዋከብ እና በማሰር ቤታቸውን በራሳቸው ፈቃድ ያፈርሳሉ ። ማፍረስ ብቻ አይደለም። ንብረትም እየዘረፉነው። ጣራ ላይ ያለ ቆርቆሮ ሳይቀር ይዘርፋሉ በማለት ነዋሪዎቹ ምሬታቸውን ለአሻራ ሚድያ ተናግረዋል።
አክለውም ማነው እንድናፈርስ ትዕዛዝ የሰጠው በማለት ብንጠይቅም፤ መልስ የሰጠን አካል የለም። ግልፅ ወረራ እየተፈፀመብን ያለ ብለዋል።
ነዋሪዎቹ እንደገለፁት ቤታችን እየፈረሰብን ያለ በማንነታችንነው በአካባቢው ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች አልፈረሰባቸውም ። እስካሁን የፈረሱት ቤቶች ሁሉም የአማራ ተወላጆች ይኖሩበት የነበሩ ናቸው።
ከአፍራሽ ግብረሃይሉ ጋር ተከትለው የሚመጡት ፖሊሶች አማርኛ መናገር የማይችሉ እና ምንም አይነት እርህራሄ የማይታይባቸው ናቸው ሲሉ ጨምረዋል ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል ።