በደራ ኦነግ ሸኔን ተዋግተው የመለሱ ሚሊሻዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደራ ኦነግ ሸኔን ተዋግተው የመለሱትን ሚሊሻዎች እስር ቤት ተወረወሩ

የደራ ጉንደ መስቀል ከተማ አስተዳደር ከላይ በመጣ ትእዛዝ ነው በሚል በቀደም ኦነግ ሸኔን ተዋግተው የመለሱትን ሚሊሻዎች በሙሉ ሰብስቦ እስርቤት ከቷቸዋል። የደራ ጉንደመስቀልን ሕዝብ ለመርዳት ከመራቤቴና ከሚዳ ወረሞ የሄዱ ፋኖዎችን መከላከያው ጦርነት ከምንገጥም ተመለሱ ብሎ መልሷቸዋል። አስተዳደሩም መንግሥት ምን እንዳሰበ አላውቅም። በኋላ በእኔ እንዳታመኻኙ በማለት የከተማው ህዝብ ከተማዋን ለቅቆ እንዲወጣ በማዘዙ የደራ ጉንደመስቀል ህዝብ አንድም ሳይቀር ከከተማዋ ውልቅ ብሎ ስደት ጀምሯል።

ኦነግ ሸኔም ከሸሸበት ተመልሶ በመንግሥት እርዳታ አሁን ወደ ደራ ጉንደመስቀል በመምጣት ላይ ነው። እስከ አሁንም ሀርቡ ደሶ፣ በቡ ድሬ፣ አዳአ መልኬ፣ ቆሮ፣ ጉንደ በርበሬ እና ኢሉ የተባሉ የገጠር መንደሮችና ቀበሌዎች በእነሱ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተረጋግጧል።

የመከላከያ ሠራዊት ደራ ጉንደመስቀል በአልፈቱ በር አፋፍ ላይ ተቀምጦ ወደታች ወደ ገደሉ በኦነግ ሸኔ የሚነደውን የገበሬ ቤት በማየት ይሳለቃል። የሃገር ሽማግሌዎች አስተዳደሩን “እሺ ከተማዋን ለኦነግ መስጠት ከፈለጋችሁ ስጡ። የታሰሩት ሚሊሻዎች ፍቱና እንደ ሕዝቡ ይሽሹ” ብለው ቢጠይቁም አስተዳደሩ ከበላይ የመጣ ትእዛዝ ስለሆነ ምንም ማድረግ አንችልም በማለቱ ሚሊሻዎቹ ሳይፈቱ ሕዝቡ ከተማዋን ለቆ ወጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀደም በፓርላማ እንደተናገሩት የወልቃይት ጉዳይ በጉልበት ከተፈታ፣ ቀጥሎ የደራ ዐማራም በጉልበት መሬቱን መውሰዱ ስለማይቀር ከወዲሁ በኦነግ ሸኔ በኩል የዐማራን ህዝብ ከደራ በማጽዳት ነገርየውን በብልጠት ለማለፍ እየሞከረ ነው የሚሉም አሉ።