በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ቀበሌ 05 ቡዳ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስተሰራ የነበረች አንዲት ሴት በሞግዚትነት የምታሳድገዉን የ11ወር ህፃን በፍሪጅ ውስጥ ከታው መገኘቱን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር አበበች ሸዋረጋ አስታውቀዋል ።
ህፃኑ በፍሪጅ ውስጥ እንደተዘጋበት የታወቀው የህፃኑ አክስት ወደ ቤት ስትገባ ህፃኑ የታለ ብላ ሰራተኛዋን ስትጠይቅ ሻወር ቤት ነው ብላ ትመልሳለች አክስት፣ ተጠራጥራ ሻወር ቤት ገብታ ስትመለከት የለም መጨረሻ አክስት የታፈነ ድምፅ ትሰማለች ፍሪጅ ስትከፍት ህፃኑ በቲማቲም ማስቀመጫ ፖላስቲክ ውስጥ ተቀምጦ ፍሪጅ ውስጥ ተዘግቶበት እንደተገኘ ኮማንደር አበበች ምርመራው ያመለክታል ብለዋል።
ሀላፊዋ እንደገለፁት የህፃኑ እናትና አባት ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አሳዳጊዋ ሰራተኛ ህፃኑ ሁል ግዜ ፍሪጅ እየከፈተ በማስቸገሩ ለማስፈራራት ብላ ፍሪጅ ውስጥ ከታው እንደነበር በወቅቱ ለደረሰችው የህፃኑ አክስት ለምን እንዲህ እንዳደረገች ስትጠይቃት መናገሯን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት እንደምትገኝና ህፃኑ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። ቤተሰብ ህፃኑ ለ2 ሰአት በፍሪጅ ውስጥ ተቀምጦ እንደነበረ ግምታቸውን ይናገራሉ በማለት ኮማንደር አበበች አክለው ገልፀዋል።
ምንጭ ፦ ሀረሪ ክልል ፖሊስ መምሪያ