የብልጽግና እና የሕወሓት ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻ እንደሚካሄድ ኢትዮጵያ በድጋሜ አስታወቀች::

የሰላም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻ እንደሚካሄድ ኢትዮጵያ በድጋሜ አስታወቀች::

በመንግስትና በህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር በአፋሪካ ህብረት ብቻ መመራት እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬዉ እለት አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬዉ ዕለት በሰጡት መግለጫ ድርድሩ ሊመራ የሚገባው በአፍሪካ ህብረት ነው ብለዋል።

ከአፍሪካ ህብረት ውጭ የሚቀርብ የእናደራድር ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት እንደሌለው ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርድሩን በገንዘብና በቴክኒክ መደገፍ እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደር መለስ፣ ከዚያ ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ነው ያሉት።

ድርድሩን የሚመሩት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦሊሰጉን ኦባሳንጆ የአደራዳሪ ኮሚቴዎችን ከአፍሪካ አገራት ማካተት እንደሚችሉም ተነስቷል።