ወልቂጤ ከተማ የሥራ ማቆም አድማ መደረጉ ተገለጸ

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሥራ ማቆም አድማ መደረጉ ተገለጸ

የጉራጌ ዞን ርዕሰ መዲና በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያዘ በዛሬው ዕለት የሥራ ማቆም አድማ መደረጉ ተገልጿል።

በሥራ ማቆም አድማው ባንኮች፣ የመንግስት እና የግል ሥራ ተቋማት፣ የንግድ እንቅስቃሴን ጨምሮ የትራንስፖርት አድማ መደረጉ ነው የተነገረው።

በአሁኑ ሠዓት ከሰብአዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውጪ ያሉ መንግስታዊና የግል እንዲሁም የንግድ ተቋማት ሥራ በማቆም ሰላማዊ ትግል ማድረግ መጀመራቸው የተነገረ ሲሆን፤ የሥራ ማቆም አድማው የአንድ ቀን መሆኑን ከነዋሪዎቹ ሰምቻለሁ ሲል ብስራት ሬድዮ ዘግቧል።

በአሁን ሰዓት በከተማዋ በርካታ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች በብዛት ተሰማርተው እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ የተናገሩ ሲሆን፤ ጉዳዩን አስመልክቶ የዞኑን የሥራ ሀላፊዎች ለማናገር የሞከረው ጥረት አለመሳካቱንም ሬዲዮ ጣቢያው ገልጿል።