ኤርትራውያን በአዲስ አበባ በከባባድ ወንጀል ላይ ተሰማርተዋል

ከመኪና ስርቆት እስከ ቤት ሰበራ ፤ ከግድያ ወንጀል እስከ ሞባይል ዘረፋ

ኤርትራውያኑ ስደተኞች ሳዋ በሰለጠኑት መሰረት ወታደራዊ ቴክኒኮችን ይጠቀማሉ

በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ኤርትራውያን መሰማራታቸውን የፖሊስ ምንጮች ለመረጃ ኮም ገልጸዋል። የፖሊስ ምንጮች እንዳሉት ኤርትራውያኑ በቡድን በቡድን በመደራጀት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ውስጥ በመሰማራት ለ24 ሰዐት በዘረፋ እና ግድያ ላይ ተሰማርተዋል። ወታደራዊ ጥበብ ያላቸው እና የሳዋ ሰልጣኞች የሆኑት ኤርትራውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ በልቅ እንዲኖሩ በመደረጉ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በመኪና ዘረፋ በተለይ የራይድ ሹፌሮችን አስገድዶና ገሎ መኪና በመንጠቅ እንደሚሰወሩ ታውቋል። የራይድ ሹፌሮችን ሲያደክሙ ውለው መኪኖቻቸውን በመንጠቅ ገለዋቸው እንደሚሄዱም በፖሊስ የተደረገው ጥናት ይጠቁማል።

በተጨማሪም በልለኢት ቤት በመስበር ባለቤቶችን በወታደራዊ ታክቲክ በመዝጋት በርካታ ንብረቶችን እንደሚዘርፉ የታወቀ ሲሆን በመንገድ ላይም በርካታ ታክቲኮችን በመጠቀም ሞባይል በመዝረፍ እንዲሁም ሰው በማይበዛባቸው ቦታዎች ሞባይል በመንጠቅ ስራ ላይ ተሰማርተዋል። ይህንን የዘረፉትን ንብረት የሚረከቡት ራሳቸው በቡን የተደራጁ ኤርትራውያን የሌባ ተቀባዮች ያሉ ሲሆን ንብረቶቹን በተለያዩ ሃሰተኛ ሰነዶች ወደ ሱዳን እና ኬንያ እንደሚወስዷቸው ታውቋል።