የተዘረጉ እጆችን ፈጣሪ ይመልከትልን #ግርማካሳ

ጎይቲቶም ገብረስላሴ፣ ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ጸጋዬ በሴቶች ማራቶን፣ በ 10 ሺህና በ 5 ሺህ ወርቅ በማስገኘት፣ ኢትዮጵጵያ በአለም አቀፍ መድረክ ከፍ ከፍ ያስደረጉ ትግራይ የተወለዱ ፣ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡
በአትሊቶቻችን ውስጤ ደስ ብሎታል፡፡ ኮርቼባቸዋልሁ፡፡ የአምስት ሺሁን ሩጫ ላይቭ ነበር ስከታተል የነበርኩት፡፡ ፈነጠዝኩ፡፡ ትንሽ ቆይቼ ግን አዘንኩ፡፡ አንዳንዶቻችን ሩጫውን ላይቭ ስንከታተል፣ ሌሎቻችንም በሶሻል ሜዲያ ስናይ፣ ደስታችንን ስንገልጽ፣ የነለተሰንበት፣ ጎይቲቱምና ግዳፍ ወለጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞች፣ ዘመድ አዝማድ፣ ያሳደጓቸው ሰፈርተኞች ግን መከታተል አልቻሉም፡፡ በትግራይ መብራት የለም፣ ኔትዎርክ የለም፣ ሁሉም ነገር ጨለማ ነው፡፡ በትግራይ ሰላም የለም፡፡ የጦርነትና የእልቁት ስጋት ብቻ ነው ያለው፡፡
እነ ለተሰንበት ሩጫቸውብ ሲቸርሱ እጆቻቸውን ወደ ፈጣሪ ዘርግተው አምላካቸውን አመስኘዋል፡፡ ምስጋና ብቻ አይመስለኝም፡፡ ልመናም ያቀረቡ ይመስለኛል፡፡ ተግራይ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን አስታውሰው፡፡ እግዚአብሄር አምላክ፣ የነ ለተሰንበትን የተዘረጉ እጆች ተመልክቶ፣ ሰላምን በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ያውርድልን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ክርዝሺህ በፊትም ብዙ ጊዜ እንደጠየኩት፣ የፌዴራል መንግስቱ በአስቸኳይ የስልክና የኤሌትሪክ አገልግሎት እንዲጀመር በአጽንኦት እጠይቃለሁ፡፡ አዎን ድርድር የሚሉት ይህ ድርድር የሚሉት ነገር አለ፡፡ ግን ይህ ድርድር ከሚባለው ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ የተበላሹ ፣ መታደስ፣ መልሶ መገንባት ያለባቸው፣ የኔትዎርክና የመብራት መስመሮች ካሉ፣ የሕወሃት መንግስት ምንም ዓይነት እክል እንደማይፈጥር ቃል ገብቶና በግልጽ አሳውቆ፣ የመብራት ኃይልና የቴሌ ሰራተኞችን ወደዚያ ተልከው በአስቸኳይ ጥገናዎችን መደረግ አለባቸው፡፡
ድርድሩ የተባለው ከተጠበቅ ችግር ነው የሚሆነው፡፡ ድርድሩ በአሁንጁ ወቅት ላይሳካም ይችላል፡፡ በጣም እየተጓተተ ነው፡፡ ኮሚቴ አዋቀርን ይላሉ፣ በአደራዳሪ ይጣላሉ፡፡ በመግለጫና በቃለ መጠይቆች እየተወጋገዙ ነው፡፡ ነገሮች የሕዝቡን ስቃይን ችግር ከግምት ባስገባ መልኩ በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ አይደለም፡፡
አሁንም የትግራይ ልሂቃን፣ የትግራይ ኃይሎች በጎንደርና በወሎ ካሉ የአማራ ኃይሎች ጋር መነጋገር እንዲጀምሩ፣ ያሉ ልዩነቶች ሁሉንም አሸናፊ ባደረገ መልኩ እንዲፈቱ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ጣጣ ማብዛት አያስፈለግም፡፡ አፍሪካ ህብረት፣ ኬኒያ፣ ኮሜቴ ወዘተ ምናምን እያሉ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም፡፡ የተወሳሰበ ፕሮቶኮል አያስፈልግም፡፡ በቀጥታ መቀሌና ባህር ዳር ያሉ ሃላፊዎች ይነጋገሩ፡፡ አስፈላጊም ከሆነ እነ አቡነ አብርሃም ንግግሩን እንዲያመቻቹ ማድረጉ ሊረዳም ይችላል፡፡ አንድ ሕዝብ ነን፡፡ ለተጋሩ ጎንደር ፣ ለአማራው አጋሜ፣ አገሩ ነው፡፡ አለቀ፡፡
እልሃችንን፣ ጀብደኝነታችንን፣ ግትርነታችንን ወደ ጎን አድርገን፣ ያለችን አንዲት አገር ናት ፣ ያቺን አገር በአትሌቲክስ ክፍ እንዳደረኛት፣ በሰላም፣ በኢኮኖሚ፣ በብልጽግና ከፍ ለማድረግ እጅ ለእጅ ተያይዘን አብረን እንስራ፡፡