በኤሌክትሪክና በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ መኪኖች በኢትዮጵያ ሊገጣጠሙ መሆኑ ተሰማ

“ድራይቭ ቴክ” የተሰኘው የኮርያ ኩባንያ በኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል በሚሰሩ መኪኖች ለመገጣጠም ነው

“ድራይቭ ቴክ” የተሰኘው የኮርያ ኩባንያ በኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል በሚሰሩ መኪኖች ለመገጣጠም የሚያስችለውን የገበያ ጥናት አጠናቋል።

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የአለም ሀገራት የተለያዩ አማራጮችን እየፈለጉ ነው።

ከዚህ ውስጥ አንዱ ከመኪና የሚወጣውን ጭስ ለማስቀረት በኤሌክትሪክና በፀሃይል ሃይል የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት ነው።

በዚህ ዘርፍ የተሰማራው ‹‹ድራይቭ ቴክ›› የተሰኘው የኮርያ ኩባንያ የኤሌክትሮኒክ ምርቶችን ለማምረት እና በታዳሽ ሃይል የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ዩን ዮንግ ቼይ ከኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር ጋር መክረዋል።

ኩባንያው ምርቶቹን ለመካከለኛው ምስራቅ እና ለአውሮፓ ሀገራት ገበያም ጭምር ለማድረስ ፍላጎት ያለው ሲሆን ፕሮጀክቱ ስራ ሲጀምር የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግና የሰው ሃይል ልማት ለመፍጠር አይነተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ ታምኖበታል።

ኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር