ሜቴክ ባቀረበው ጥራት የጎደላቸው የሐይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ገመዶች ምክንያት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ላይ መስተጓጎል አስከተለ፡፡

በሜቴክ በኩል የቀረቡት የሐይል ተሸካሚ ገመዶች የጥራት ጉለት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል

(ኢፕድ)
ሜቴክ ባቀረበው ጥራት የጎደላቸው የሐይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ገመዶች ምክንያት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ላይ መስተጓጎል አስከተለ፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ትራንዚት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ እንደገለጹት የቀላል ባቡር ትራንስፓርት በሚፈለገው ደረጃ ስራውን እንዳያከናውን በሜቴክ በኩል የቀረቡት የሐይል ተሸካሚ ገመዶች የጥራት ጉለት ምክንያት በአገልግሎት አስጣጡ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል ፡፡

የሐይል ተሸካሚ ገመዶች ዝርጋታ በዋናነት የተከናወነው ሜቴክ በሚያቀርባቸው እና ዲኤም ሲ ከተባለ የቱርክ ኩባንያ ሲሆን በሜቴክ በከኩል የተከናወነው 15ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡

በሜቴክ የተዘረጉ መስመሮች ከሀያት ለም ሆቴል እና ከቃሊቲ መሷለኪያ ናቸው ፡፡የባቡር መቆም ሆነ የሐይል መቆራረጥ እየተከሰተ ያለው በዚሁ መስመር ላይ መሆኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል፡፡

ሞገስ ተስፋ