የቢቢኤን ጋዜጠኞች እና የድምፃችን ይሰማ አክቲቭስቶች የሆኑት ሳዲቅ አህመድ እና አብዱራሂም አሕመድ አዲስ አበባ ገቡ

የቢቢኤን ጋዜጠኞች እና የድምፃችን ይሰማ አክቲቭስቶች የሆኑት ሳዲቅ አህመድ እና አብዱራሂም አሕመድ አዲስ አበባ ገቡ
በውጭ ሃገራት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ድምጽ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ቢቢኤን (በረካ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ) የመገናኛ ብዙሃን መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ገብተዋል።
 
የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች የሙስሊም ማሀበረሰብ ክፍሎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የቢቢኤን ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ አህመድ እንደተናገሩት፤ ቢቢኤን ባለፉት ሰባት አመታት መሰረቱን በአሜሪካ በማድረግ የሙስሊም ማህበረሰብ ንቅናቄው መሪዎችን ድምጽ በማስተጋባትና ወጣቶች ወደ አላስፈላጊ ግጭቶች ውስጥ እንዳይገቡ ሲሰራ ቆይቷል።
 
በውጭ አገሮች የሚገኙ የሀይማኖት መሪዎችና ኢትዮጵያውያን በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን የጋራ መድረኮችንም በማዘጋጀት አንድነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።
 
“ላለፉት ሰባት አመታት ወደ አገራችን መግባት አንችልም ነበር በአሁኑ ወቅት ግን በአገሪቱ በመጣው ለውጥ ወደ የምንወዳት አገራችን በመምጣታችን ልዩ ደስታ ተሰምቶናል” ሲሉም አቶ ሳዲቅ ተናግረዋል።