በት/ቤቱ ረብሻው የተነሳው የኦሮምያን የክልል ባንዲራ “እንሰቅላለን” በሚሉ ኃይሎች እና በሚቃዎሙት የአዲስ አበባ ተማሪዎች እንዲሁም መምህራን መካከል መሆኑ ተገልጿል።
በረብሻው ምክንያት እስካሁን ድረሰ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን የትምህርት ስራው ቆሞ መዋሉን በአካባቢው የሚገኙ የተማሪ ወላጆች ገልፀዋል።
ገላን ልዮ የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሆኑ ይታወቃል።በዚህ ዓመት ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በከተማ አስተዳደሩ እንደተበጀተለት የመረጃ ምንጮች ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጅ እንደ ወላጆች ገለፃ እና ባገኘነው የሰነድ ማስረጃ መሰረት ከሆነ በት/ቤቱ 97% የሚሆኑት መምህራን እና ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የኦሮምያ ከተሞች የመጡ ናቸው።
የተቀሩት 3% የሚሆኑት ደግሞ ከአዲስ አበባ የገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።አንደ መረጃ ምንጮች ከሆነ በየጊዜው በት/ቤቱ አስተዳደር በተማሪዎች እና መምህራን ላይ በሚደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት የአዲስ አበባ ተመሪዎች እና መምህራን አየለቀቁ ነው ብለዋል።
ካሰው መርጋ የተባሉ ግለሰብ በሚመሩት አዳሪ ት/ቤት ውስጥ የሚገኙት የአስተዳደር ሰራተኞች እና አብዛኛው መምህራን የትምህርት ማስረጃ የሌላቸው ነገር ግን በማንነታቸው ብቻ የመጡ ናቸው።ተብሏል።
የዛሬውን ረብሻ ተከትሎ የክፋለ ከተማው አስተዳደር እና ት/ቤቱ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ የገዳ መዝሙር እንዲዘመር እና የኦሮምያ ክልል ባንዲራ በት/ቤቱ እንዲሰቀል ተወስኗል ብለዋል መረጃ ሰጭዎቻችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል ።