ኢትዮጵያ ግብፅን አሸንፋ ምድቡን መምራት ጀመረች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የተደለደለበትን ምድብ መምራት ጀመረ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማላዊ ላይ የግብፅ አቻውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው ያሸነፈው። ዋሊያዎቹ ፈርዖኖቹን 2 ለ 0 ያሸነፉት በመጀመሪያው አጋማሽ ዳዋ ሁጤሳ እና ሽመልስ በቀለ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው።…