ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የጣለችውን የሰዐት እላፊ አስረዘመችው

በማርሳቢት የተጣለው ሰዓት እላፊ ተራዝሟል።

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ ማርሳቢት የተጣለው የሰዓት እላፊ በ30 ቀን እንዲራዘም መወሰኑን የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የኬንያ መንግሥት በማርሳቢት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ማሰማራቱና ለአንድ ወር የሰዓት እላፊ አዋጅ ማወጁ እንዲሁም ትጥቅ እንደሚያስፈታም መግለፁ አይዘነጋም።

ከሳምንታት በፊት በማርሳቢት ከተማ አረመኔያዊ የተባለ ግድያ መፈፀሙ በዚህም የአካባቢው አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎችም መገደላቸው ይታወሳል።