ኢትዮጵያ ወደ ነዳጅ ሃብት ምርት ገብታ ተጠቃሚ ለመሆን እስከ ሶስት ዓመት እንደሚፈጅባት ተነገረ

ወደ ነዳጅ ምርትና ሽያጭ ለመግባት እስከ ሶስት ዓመት ይጠይቃል


ኢትዮጵያ ወደ ነዳጅ ሃብት ምርት ገብታ ተጠቃሚ ለመሆን እስከ ሶስት ዓመት እንደሚፈጅባት የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የነዳጅ ፈቃድና አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር ቀፀላ ታደሰ በአሁኑ ወቅት ነዳጅ በተገኘባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ ጥናት በማድረግና በሌሎች ቦታዎች በመፈለግ ደረጃ ላይ ነን ብለዋል።

ቀደም ሲል በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ ከ4 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በላይ የተገኘ ቢሆንም አሁን ያለበት ደረጃ ለምን አይነት አገልግሎት ቢውል እንደሚያዋጣና ለማንና እንዴት መሸጥ እንዳለበት ጥናት በማድረግ ላይ ነን ሲሉ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE