“አንቱ በእናቱ”፡ የኢትዮጵያዊው ምርኮኛ እና የኤርትራዊቷ ታጋይ የፍቅር ታሪክ

አቶ ማሞ አፈታ በባለቤታቸው ሕይወት ተስፋይ ፍቅር የተማረኩበትን አጋጣሚ ሲናገሩ ‘ትጥቋና አስተጣጠቋን’ ያነሳሉ። ኢትዮጵያ የኤርትራ ነጻ አውጪዎችን ጦርነት በገጠመችበት ወቅት የተማረኩት አቶ ማሞ፣ የልባቸው ሜዳ ላይ ፍቅር የበቀለው እዚያው በምርኮ ሳሉ ነው። ከማረኳቸው የሻዕብያ ወታደሮች መካከል መልከ መልካሟን ሕይወት ተስፋይን ተመለከቱ። የልባቸው በር ወለል ብሎ ተከፈተ።…