የትዉልድ ክፍተት፤ የሌንጮ ምልከታ

የትዉልድ ክፍተት፤የሌንጮ ምልከታ


የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሥልጣን የያዘዉ ትዉልድ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ በ1960ዎቹ ፖለቲካዉን ከተቀየጠዉ ነባር ኢትዮጵያዊ ትዉልድ አስተሳሰብ በጣም የተለየ እንደሆነ አንጋፋዉ ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ መሠከሩ።

በ1960 አጋማሽ የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ)ን የመሠረቱት እና አሁን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ)ን የሚመሩት አቶ ሌንጮ ለDW እንደነገሩት በሥልጣን ላይ ያለዉ ትዉልድ ከቀድሞዎቹ ይልቅ ታጋሽ፤ቻይ እና ለዴሞክራሲ ግንባታ የሚረዱ ፀባያት (ባሕሪዎች) አለዉ።

አቶ ሌጮ «እንደኔ ዓይነቱ» ያሏቸዉ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኞች ግን ከቀድሞዉ አስተሳሰባቸዉ ምንም አልተለወጡም።«ልክ እንደ ድሮዉ ናቸዉ፣ ሐሳባቸዉም አረማማዳቸዉም።» ይላሉ አንጋፋዉ ፖለቲከኛ።አቶ ሌንጮ ለታ በምክትል ሊቀመንበርነት ይመሩት የነበረዉ የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) በ1983 በተመሰረተዉ የሽግግር መንግስት ዉስጥ ከኢሕአዴግ ቀጥሎ ትልቁ የፖለቲካ ድርጅት ነበር።

ይሁንና ብዙም ሳይቆይ የሽግግር መንግሥቱን ጥሎ ሲወጣ አቶ ሌንጮም ከሐገር ተሰደዉ፤ ከኦነግም ለቅቀዉ አዲሱን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን (ኦዴግ)ን መሥርተዉ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከጥቂት ወራት በፊት ነዉ።ኦዴግ ከኦሮሚያ ገዢ ፓርቲ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ጋር ለመዋሐድ ትንንት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

DW Amhaic


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE