የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያላቸው አመለካከት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያላቸው አመለካከት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሴቶች ፖለቲካ ውስጥ እንዳይገቡ በግልጽ ‹‹የማስፈራራት፣ የማሸማቀቅ፣ ነውር ድርጊት›› እንደሚፈጽሙ፣ ያጋጠሙት ሁኔታዎች የሚያስደነግጡና የሚያሳዝኑ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡