የሩሲያ ነዳጅ እና የአውሮፓ ኅብረት ስድስተኛ ማዕቀብ

የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት በሩሲያ ላይ ስድስተኛ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የኅብረቱ የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ኃላፊው እንዳሉት ማዕቀቡ ተጨማሪ የሩሲያ ባንኮችን ስዊፍት ከተባለው ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓት ለማገድን ይጨምራል። ሩሲያ ለኅብረቱ የምታቀርበው ነዳጅ ሌላው የማዕቀቡ ዒላማ ነው።…