![](https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2022/05/279377079_573765380981388_9038697507034714351_n-296x300.jpg)
የባልደራሱ ቢንያም ታደሰ በድጋሜ ታሰረ
/
የአድዋና የካራማራ የድል በዓላትን ሰበብ በማድረግ ከአንድ ወር በላይ በግፍ በአባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት ታስሮ የቆየው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባሉ ቢንያም ታደሰ በድጋሜ በፖሊስ መታሰሩን ባልደራስ በፊስ ቡክ ገጻኡ አሳውቋል፡፡ ወጣት ቢንያም ታደሰ ከሰሞኑ በጎንደር እና በስልጤ አካባቢዎች የእምነት ተቋማት ላይ እየደረሰ ያለውን ሃይማኖታዊ ጥቃት ሲያወግዝና አንድነትን ሲሰብክ እንደነበረ ያሳወቀው ባልደራስ፣ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ፣ በቀድሞው ማዕከላዊ ይባል በነበረውም 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በፖሊስ ኮሚሽን መታሰሩ ገልጿልLL