![](https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2022/04/afar-300x169.jpg)
![](https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2022/04/IMG_5090-2-300x200.jpg)
የአብይ አህመድ የኦህዴድ/ብልጽግና መንግስት ላለፉት 4 አመት አገሪቷን ሲመራ ለአገር ያመጣው ነገር ቢኖር፡
– ብልጽግናን ሳይሆን የድህነትና የኑሮ ውድነት ጥግን እና ረሃብን፣
– መደመርንና ሳይሆን መከፋፈልን ፣ ልዩነትንና መቀነስን፣
– የዜጎችን ደህንነት፣ ወጥቶ በሰላም መግባት ሳይሆን የዜጎችን ጭፍጨፋ፣ እልቂት፣ መፈናቀልን፣
– ሰላምንና መረጋጋት ሳይሆን ጦርነትንና ሽብርን፣
– እኩልነትን ሳይሆን ተረኝነት፣ ልዩ ጥቅም በሚል የአንድን ጎሳ የበላይነት ማስፈንን እና በሕወሃት ጊዜ ከነበረው የባሰ ዘረኝነትን፣
– ፍትህን ሳይሆን የዱርዬ ፍትህ አልባ ፣ ህገ አልባ አሰራርን፣
– መልካም አስተዳደርን ሳይሆን የለየለት ሌብነትንና መንግስትዊ ዝርፊያን
– የሰለጠነ ዘመናዊ ፖለቲካን ሳይሆን የዘርና የኃይማኖት አክራሪነትን
– አገርን ማስከበር ሳይሆን አገርን በአለም አቀፍ መድረክ ማዋረድን
– ልማትን ሳይሆን ውድመትን
– አንድነትን ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሳይሆን ጎጠኝነትን፣ ጸረ ኢትዮጵያዊነትን
– ዲሞክራሲን ሳይሆን የለየለት አፈናንና አምባገነናዊነትን
ነው፡፡
ትግራይ ሄዱ፣ ኦሮሞ ክልል እነ ወለጋ ሂዱ፣ አማራ ክልል ሂዱ፣ አፋር ክልል ሂዱ ፣ ደቡብ ክልል ሄዱ ….ከተለያይ ጎሳዎች ወይንም ኃይማኖቶች ይሁኑ፣ “አሁን ያላችሁበት ሁኔታ ነው ወይስ ከአራት አመት በፊት የነበራችሁበት ሁኔታ ነው የሚሻላችሁ ?” የሚል ጥያቄ ብታቀርቡላቸው፣ ከ 4 አመት በፊት የነበረው በአስር እጥፍ እጥፍ ይሻል ነበር የሚል መልስ ነው የሚሰጧችሁ፡፡ አማራው፣ ትግሬው፣ ኦሮሞው፣ ወላይታው፣ ጉራጌው….፣ ዉህድ ኢትዮጵያዊው ፣ ሙስሊሙ፣ ክርስቲያኑ ሁሉም እያማረረ፣ እያለቀሰ ነው፡፡
ምን አልባት ከጥቂት ዘራፊና ሌባ የኦህዴድ/ብልጽግና ሰዎች፣ ለኦህዴድ ታዛዥ የሆኑ የሌሎች ክልል የብልጽግና ቅርንጫፍ አብሮ ሰራቂና ዘራፊ ሌቦ አመራሮች፣ እንዲሁም ከገዢው ብልጽግና ጋር ጥቅምና እንደ ቦርድ አባልነት ያሉ ስልጣን ካገኙ ተደማሪ ተለጣፊዎች ውጭ፣ በሁሉም የአገሪቷ ክፍል የሚኖረው ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ፣ ኑሮ አማሮት፣ እየተሰቃየ፣ እየተፈናቀለ፣ የዘመኑ ተረኞች የግፍ ዱላ እያረፈበት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ ሆኖ፣ የአብይ መንግስት ችግሮቹን externalize እያደረገ፣ ላይ ላዩን ፍቅርና መደመር እያለ፣ ውስጥ ውስጡን ግን በተግባር እርስ በርስ እያጣላ፣ እንደ አስታራቂ ሆኖ ለመቅረብ እየሞከረ ነው፡፡ ዶር አብይና የብልጽኛ ስዎች ሙስሊሙ ጋር አንደኛ ሙስሊም ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ክርስቲያኑ ጋር አንደኛ ክርስቲያን ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ኃይማኖትን እንደ ፖለቲካ ካርድ እየተጫወቱ፡ ለአማራው፣ “ያስቸገሩን ኦነግ ሸኔዎች ናቸው” ብለው እነርሱን ከተጠያቂነት ነጻ አውጥተው ኦነግ ሸኔ የሚሉት ላይ ጣት ይቀስራሉ፡፡ በጓዳ ከሕወሃት ጋር እየተደራደሩ፣ እየተቃቀፉ፣ በፊት ለፊት ግን አማራው ጋር መጥተው፣ ሕወሃትን ይረግማሉ፡፡ ለኦሮሞው ፣ “ያስቸገረን ፋኖ ነው” ይላሉ፡፡ በፊት አብን ነው ይሉ ነበር፣ አሁን አብንን በኪሳቸው ስላስገቡት አብን ማለት አቁመዋል፡፡ ፋኖን እንደ ጠላት በማቅረብ፣ እኛ ከሌለን ፋኖ ያጠፋቹሃል ብለው ኦሮሞውን ያስፈራራሉ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ባልደራስን እየከሰሱ እንደ ጽንፈኛ እያቀረቡ ነው፡፡ ትግሬዎቹ ጋር ይሄዱና በውስጥ መስመር ፣ “ያስቸገሩን አማራዎች ፣ በተለይም ጎንደሬዎች ናቸው፡፡ የነርሱን ነገር አንድ ካደረግን በኋላ ወልቃይትን እንሰጣቹሃለን” ይላሉ፡፡ ለአንዱ አንድ ታሪክ፣ ለሌላው ተቃራኒዉን እየተናገሩ፣ እያወናበዱ፣ እያታለሉ፣ አገርን ወድ ከፋ ደረጃ እየወሰዷት ነው፡፡
ኢትዮጵያዉያን መጠየቅ አለብን፡፡ ከአራት አመት በፊት አሁን እንደምናየው በኃይማኖት በዘር ግድያዎች ነበሩ ወይ ???? ያኔ የነበረው ሕዝብ ነው አሁንም ያለው፡፡ ያኔ የነበረ ኦሮሞ ፣ ትግሬ፣ አማራ …ነው አሁንም ያለው፡፡ ያኔ የነበረው ሙስሊም ፣ ክርስቲያን ነው አሁንም ያለው፡፡ ህዝቡ ያው ነው፤፡ ታዲያ አሁን እያየን ያለው ደም መፋሰስና እልቂት ለምን በዛ ???????
ጎበዝ ችግሩ ያለው ሕዝቡ ጋር ሳይሆን አራት ኪሎ የተቀመጠው፣ ክፉ፣ የበሰበሰ፣ ዘረኛ፣ ለሕዝብ ስቃይ ደንታ የሌለው፣ ራሱን ብልጽግና ብሎ የሚጠራው፣ ውሸት ላይ የተመሰረተው፣ ተረኛ አገዛዝ ጋር ነው፡፡ ይህ አገዛዝ የሚቀበለውና በአምስተኛ ማርሽ እያስቀጠለ ያለው የጎሳ ፣ የመከፋፈልና የልዩነት ሕገ መንግስትና የዘር ፖለቲካ ጋር ነው፡፡
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦህዴድ የጨለማ አገዛዝ፣ አገርን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ አይደለም፣ አገር እየገሰገሰችበት ካለው የጥፋትና የእልቂት የቁልቁለት ጉዞ ማስቆም አልቻለም፡፡ ማስቆም አይደለም እንደውም የበለጠ ፍጥነቱ እንዲጨምር እያደረገ ነው፡፡
ለዚህ ነው ይህ አገዛዝ በአስቸኳይ መቀየር አለበት የምንለው፡፡ አብይ አህመድ የሚወደውን የአትክልት ስራ በሙሉ ጊዜው እንዲሰራ ከሃላፊነቱ ይነሳና ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ይቋቋም፡፡
አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እርሱን ጉዳይ ይመለከተዋል ብላችሁ አታስቁኝ፡፡ ይህ ኮሚሽን እንደተወለደ የሞተ ኮሚሽን ነው፡፡ የሚፈይደው ሆነ የሚያመጣው ምንም ነገር አይኖር