የደቡብ ክልል ልዩ ሀይልና የኮንሶ ፖሊሶች ጥምረት በጉማይዴ ሰገን ከተማ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጅምላ እስር ጀምረዋል !

ከትላንት የጀመረው የደቡብ ክልል ልዩ ሀይልና የኮንሶ ፖሊሶች ጥምረት በጉማይዴ ሰገን ከተማ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጅምላ እስር ጀምረዋል !

እስካሁን ከተማውን ለቀው ከወጡት ወጪ የሰገን ደብረመዊዕ ቅዱስ ገብር ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቄስ ታደለ ደነቀን ጨምሮ እስከ ትላንት ብቻ በቁጥር 80 በላይ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ታስረዋል።

ከጅምላ እስረኞቹ መካከል አጥቢ እናቶች ከእነ ልጆቻቸው፣ ሽማግለዎቼና ወጣቶችም ይገኙበታል። ከእስር የቀሩት የእስረኞቹ ቤተሰቦች ለእነዚህ የግፍ ታሳሪዎች ምግብ እንኳን እንዳናስገባ ተከልክለናል ያሉ ሲሆን የአይን እማኞቹ እንደገለጹት በጠባቧ እስርቤት ውስጥ ከፍተኛ የሕፃናት ጩሄትና የእናቶች ለቅሶ ይሰማል ተብሏል።

ባለፈው የዱጋያ ማርያም ቤተክርስቲያን ተዘርፎ የጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት ምንም ነገር ባለማለቱ ትላንት የሰገን ገብርኤል ቤተክርስቲያን ለማዘጋት የደብሩን አስታዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ከአራት ቤተሰቦቻቸው ጋር ወስደው አስረዋል።

ከትላንት የጀመረው የደቡብ ክልል ልዩ ሀይልና የኮንሶ ፖሊሶች ጥምረት በጉማይዴ ሰገን ከተማ ሕዝብ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ እስር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በኮንሶ በኩል ወደ ሰገን ከተማ በሚመጡት ታጣቂዎች የጥይት ድምጽ መታወኩን እንደቀጠለ ነው። መንግስት ለአካባቢው ምንም ትኩረት ባለመስጠቱ በየቀኑ የአርሶአደሮች ሞት የተለመደ ሆኗል። ትላንትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃን በዚሁ ሀይል መገደላቸው ከስፍራው ባገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።