በቴፒ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ወጭ ናቸዉ ተባለ

[addtoany]

በደቡብ ከልል ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ከአራት ወራት በፊት በተነሳ አለመረጋጋት ከኬጂ ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ካምፓስ ትምህርት መስጠት አልጀመሩም ።

በሚያሳዝን መልኩ በአስር በሺሆች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ወጭ ናቸዉ። የአስተዳደር መዋቅሩም ፈርሶ መስሪያ ቤቶች ስራ ካቆሙ አራት ወር አለፈው። ሰዎች በየቀኑ እየሞቱ ነው።

የክልሉ መንግስትም ተገቢውን ትኩረት እየሰጠው አይደለም። ሁኔታው የዘር እልቂት እንዳያመጣ ያሰጋል። መንገድ ተዘጋግቶ ከቤት መውጣት ካቆምን አስር ቀን ሞላን ሰው በርሀብ ሊያልቅ ነው ብለዋል የከተማው ነዋሪዎች ።