የሰላም አማራጭ የማይኖር ከሆነ፣ የትግራይ ምድር ሲኦል ያደረገውን እገታ ለመስበር ወደ ሌሎች አማራጮቻችንን በድጋሚ ለመመለስ እንገደዳለን -ዶ/ር ደብረፅዮን

ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው አካል መሪ የሆኑትና የክልሉ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ ግልጽ ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡

በድርጅቱ የግንኙነት ገጽ ላይ ባሰፈሩት ባለ 4 ገጽ ደብዳቤያቸው፣ በኢትዮጵያ፣ “በሁሉም ዘርፍ እያሽቆለቀለ ነው” ያሉትን አሳሳቢ ሁኔታ ዘርዝረዋል፡፡

በትግራይ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደ ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ የሚችል አለመሆኑን ጠቅሰው መንግሥታቸው ለሰብአዊነት ሲባል ሰላም ለማውረድ ቢስማማም በሌላ ወገን የተገባው ቃል ተግባራዊ አለመደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ደብረፅዮን በማጠቃለያቸው፣

“የሰላም አማራጭ የማይኖር ከሆነ፣ የትግራይ ምድር ሲኦል ያደረገውን እገታ ለመስበር ወደ ሌሎች አማራጮቻችንን በድጋሚ ለመመለስ እንገደዳለን”ብለዋል፡፡