ኢየሩሳሌም የሚገኘው የኢትዮጵያ ርስት ዴር ሱልጣን ገዳም በግብፃውያን መነኮሳት የወረራ ሙከራ እየተደረገበት ይገኛል

No photo description available.በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘው የኢትዮጵያ ርስት ዴር ሱልጣን ገዳም በግብፃውያን መነኮሳት የወረራ ሙከራ እየተደረገበት ይገኛል !!!
የግብፅ መነኮሳት ትናንት ሚያዚያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ላይ በዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ግቢ ውስጥ በኃይል በመግባት ወረራ የፈፀሙ ቢሆንም በገዳሙ በሚኖሩ አበው መነኮሳት እና ጥሪውን ሰምተው በተሰባሰቡ ምዕመናን ብርቱ ትግል በውሃላ ከግቢ ቢወጡም ሌሊት የኢትዮጵያ ገዳም ዴር ሱልጣን በር ላይ የግብፅን ባንዴራ በቀለም ስለው አድርዋል።
በተጨማሪም ግቢ ውስጥ የሽቦ ገመዶችን በመወጠር ተጨማሪ ባንዲራ ግቢ ውስጥ ለመስቀል እየተንቀሳቀሱ መቆየታቸው ነው የተገለፀው።
በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ርስት ገዳም በመምጣት አባቶቻችን በብዙ መሰዋዕትነት ሰርተው ያቆዩልንን ርስት ተገኝተን መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉ በርካታ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
No photo description available.