በኦነግ ጥቃት ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ የሚወስደው መንገድ እንደተዘጋ ነው

May be an image of 2 people and roadየኦነግ ሸኔ ቡድን ከሸዋሮቢት በቅርብ ርቀት ጀጀባ ዙጢ ባሉ ኬላ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ተከትሎም ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ የሚወስደው መንገድ መዘጋቱን ተጓዦች ተናግረዋል።
ብዙ ሰዎች ከጀጀባ ዙጢ ተፈናቅለው ወደ ሸዋሮቢት በእግራቸው ሲገቡ ተስተውሏል። ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ቤተ አምሐራ ወሎ ደሴ ሲጓዙ የነበሩ ተጓዦች ለአሚማ እንደገለጹት ደብረሲና ላይ ቆመው ይገኛሉ፤ በሸዋሮቢት ችግር አለ በመባሉ ብዙ ተሽከርካሪዎች ቆመው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ብለዋል። ለአማራ ሚዲያ ማዕከል
ከሚያዚያ 7/2013 ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ እና አካባቢውን ነዋሪዎች ላይ የጅምላ ፍጅት በመፈጸም አጣዬ ከተማን ሙሉ በሙሉ ያወደመው የመንግስት አካላት ድጋፍ እንዳለው በተደጋጋሚ የሚነገርለት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን መሆኑ ይታወቃል።
May be an image of 4 people, bus and outdoorsይህ የቡድን መሳሪያ ጭምር በንጹሃን ላይ የሚተኩስ ወራሪ ቡድን በተመሳሳይ በዓመቱ ሚያዝያ 9 እና 10/2014 በሁለት ወረዳዎች ማለትም በኤፍራታ ግድም እና በሸዋሮቢት ቀወት ወረዳ በ3 ቀበሌዎች ጥቃት መክፈቱን ለማወቅ ተችሏል።
ሚያዚያ 9/2014 ከቀኑ 11:30 እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ በአጣዬ ዙሪያ ኤፍራታ ግድም ወረዳ ሞላሌ ቀበሌ ነጌሶ አካባቢ እንዲሁም በሸዋሮቢት ቀወት ወረዳ ኩሪብሪ አካባቢ ጥቃት ከፍቶ ማምሸቱ ተገልጧል።
በዚህም አሚማ ለማጣራት እንደሞከረው እስካሁን አንድ ህዝባዊ ፖሊስ ተገድሏል፤ የቆሰሉ አሉ፤ ንብረት ስለመውደሙም ለማወቅ ችሏል።
በተመሳሳይ የታወቀ ማሰልጠኛ፣ደጋፊ እና የመንቀሳቀሻ አካባቢ ያለው የሽብር ቡድኑ ሚያዝያ 10/2014 ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ በሸዋሮቢት ጀጀባ ዙጢ በተባለ አካባቢ ኬላ ላይ በነበሩ የጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍቷል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ