የአሜሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ሪፖርትና የኢትዮጵያ ምላሽ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች በ2021 የነበረውን ይዞታ የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ይኸ ሪፖርት በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ዘርዝሮ ያቀረበ ነው። በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራና ክትትል ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታ ሪፖርቱን “ከሞላ ጎደል ጥሩ ሊባል የሚችል” ብለውታል…