# “እናንተ ለብዙ ዓመታት በልታችኋል፣ አሁን ተራው የእኛ ነው” የመንግሥት ባለስልጣን የተናገሩት!
# ቤቶች ኮርፖሬሽን አንበሳ ፋርማሲና ኒኦን አዲስ አይፈርሱም አለ፣ ውል ያቋረጠው ግን ከህግ ውጭ ነው!
/
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አንበሳ ፋርማሲ እና ኒኦን አዲስ እንዲፈርሱ አልተወሰነም ሲል አስተባበለ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ባወጣው መግለጫ፣ “አንበሳ ፋርማሲ እና ኒኦን አዲስ የተባሉ ድርጅቶች በኪራይ ሲገለገሉበት የነበሩት እና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑት ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶቹ የቅርስነት ይዞታቸው ሳይቀየር ባሉበት ምንም ዓይነት የቅርስነት ይዞታቸው ሳይቀየሩ አስፈላጊውን እድሳት እና እንክብካቤ እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል…በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውሳኔ ቤቶቹ የቅርስነት ይዞታቸው ሳይቀየር…በአካባቢው ከሚገነባው አዲስ ግንባታ ጋር ለአልሚ አባላት እንዲተላለፉ ከማድረግ ውጭ በቅርሶቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አይደርስባቸውም ” ብሏል፡፡
ሆኖም፣ ቤቶቹ የማይፈርሱ ከሆነ ያለምንም ምክንያት ከአንዱ ተከራይ ወደ ሌላ ተከራይ በምን የህግ አግባብ እንዲተላለፍ እንደተወሰነ ኮርፖሬሽኑ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ ሆኖም፣ ከዚህ በፊት አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አሁን ላሉት ተከራዮች በንዴት ሲናገር፣ “እናንተ ለብዙ ዓመታት በልታችኋል፤ አሁን ደግሞ የእኛ ተራ ነው” በማለት እንደተናገራቸው ይታወሳል፡፡
አሁን ያሉት ተከራዮች ያለ ምንም ምክንያት ውጡ ተብለው ቤቶቹ ለናዝሬት ከተማ ባለሀብቱ ጀርመን አመንቴ መዘዋወራቸው የባለሥልጣኑ አባባል ትኩረት እንዲሰጠው የሚያደርግ ነው።
/
/
(ምንጭ ባልደራስ)