በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ዉድነቱ ሰዎችን ወደ አመፅና ዘረፋ እንዳያስገባ ያሰጋል

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ የመጣዉ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ሕዝቡን ክፉኛ እያስጨነቀ፣ አንዳዶችን ደግሞ ለተመፅዋችነት እየዳረገ ነዉ።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት በተራዉ ዜጋና በባለስልጣናት፣ በድሆችና ሐብታሞች መካከል የሚታየዉ እጅግ የሰፋ የኑሮ ተባለጥ ችግረኞች የአመፅና ዘረፋ አማራጭን እንዲያማትሩ እያስገደደ ነዉ።የንግድና ቀጠናዊ ሚንስቴር ትናንት ለሐገሪቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች ባቀረበዉ ዘገባ ግን ችግሩን «ዉጪያዊ» አድርጎ አቅርቦታል።አንዳድ የምክር ቤት አባላት ግን የችግሩን ጥልቀት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠንከር ባሉ ቃላት ሲገልፁና መንግስትን ሲያስጠነቅቁ ተሰምተዋል።