የሕዝብ ብሶት በሕዝባዊ ውይይት መድረኮች

‹‹አገር ውስጥ ሲመረት እናያለን፡፡ ከውጭ አገርም ሲገባ እናያለን፡፡ ይህ ሁሉ ምርት ወዴት እየሄደ ነው በየገበያው ሸቀጥ የለም የምንባለው?›› በማለት ነበር የአዳማ/ናዝሬት ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንዲት እናት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን አቶ ሽመልስ አብዲሳን በጥያቄ ያፋጠጡት፡፡ እኚህ እናት የፖለቲካ ካድሬና ኢኮኖሚስቱ በየሚዲያው ልራቀቅበት የሚለውን የአቅርቦትና የፍላጎት መሠረታዊ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሐሳብ ለምን እንዳልሠራ በአንዲት ዓረፍተ ነገር በቀላሉ ጠይቀዋል፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአቅመ ፖለቲካ አልደረሰም ለሚለውና ሕዝብን ያታለለ ለሚመስለው ጥቂት የፖለቲካ ልሂቅ አስተማሪነቱ ሳይጠቀስ የማይታለፍ መሆኑ ብዙዎችን ያስማማል፡፡

የሕዝብ ብሶት በሕዝባዊ ውይይት መድረኮች | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic