ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን በተመለከተ ለኦፌኮ መግለጫ መልስ ሰጡ

የዛሬው የብልፅግና ጠቅላይ ሚኒስትር መልዕክት የሕዝቡ እምነት በመንግስት ላይ መሸርሸሩን በቂ ማሳያ ነው። የምክክር መድረኩ እኮ በመንግስት የተደራጀ የቅጥረኞች ሕብረት ሲሆን ኮሚሽነሮችም የዕርቀ ሰላምና የወሰን ማካለል ኮሚሽኖችን ያከሸፉ የመንግስት ታዛዦች ናቸው። ጠቅላዩ በየመድረኩ የሚናገሩት በራሱ እንኳን ለሃገራዊ ምክክር አይደለም ለማሰብም አይጋብዝም። የጠሚው መልዕክት ለኦፌኮ መግለጫ መልስ ነው።

ብልጤው ጠሚው የብሔራዊ ምክክሩ አሳታፊነት የሚሳካው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀናነትና በባለቤትነት ሂደቱን መደገፍ ሲችል ነው ብለዋል። አሁንም ሕዝብ ያምንነናል ብለው ያስባሉ። ካድሬዎቻቸውና ተከፋይ አክቲቪስቶቻቸው ስላጨበጨቡ ብቻ በሞቅታ የሚሰጥ መግለጫ ምንም ውጤት የለውም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በባለቤትነትና በቀናነት እንዲደግፍ እኮ መጀመሪያ መንግስት መኖሩ በተግባር ሊረጋገጥ ይገባል። የመንግስት ባለስልጣናት ከማውራት ውጪ በተግባር የሰሩት ስራ የለም። ጥቂት ነገርን አካብዶና አግዝፎ ማውራት ለትዝብት ይዳርጋል።

ታንኩም ባንኩም በጃችን ነው በሚል የተረኝነት ፈሊጥ የምታወሩት ሌላ የምትሰሩት ሌላ ሆኖብን ነው እኮ የተቸገርነው። በሁሉም ነገር ላይ ሕዝቡ እምነት አቷል። አይገባችሁም እንዴ ? ሕዝቡ ዝም ሲል የተስማማ መስሏቹ ከሆነ ስሕተት እየሰራችሁ ነው። ለውጡ ተቀልብሷል። ተረኝነት ነግሷል። እምነት ጠፍቷል።

የምክክር መድረኩ ሰዎች ካሁን በፊት በመንግስት ተወልደው በመንግስት የተገደሉ የመንግስት ኮሚሽኖች አባላትን ያሳተፈ ከመሆኑም በላይ የከሸፉ የመንግስት ደጋፊዎችን ይዞ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ማሰብ አስቂኝ ነው። ጠቅላዩ በየመድረኩ የሚናገሩት በራሱ እንኳን ለሃገራዊ ምክክር አይደለም ለማሰብም አይጋብዝም። በአጠቃላይ የዛሬው የጠቅላዩ መልዕክት ለኦፌኮ መግለጫ መልስ ነው። #MinilikSalsawi