አሜሪካ ኤርትራ ከ25 ዓመት በፊት ያረቀቀችውን ሕገ መንግሥቷን ተግባራዊ እንድታደርግ፣ ነጻ ምርጫ እንድታካሂድ እና ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጡ እንድትፈቅድ አሥመራ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ጠይቃለች።
ኤርትራ ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች እስር ቤት የሚወረወሩባት አገር ሆና መቀጠሏ እንደሚያሳስባት አሜሪካ ገልጻለች። የአሜሪካ ኢምባሲ ይህን ያለው፣ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገ/መስቀል የአሜሪካ የምርጫ ሥርዓት በገንዘብ የሚዘወር መሆኑን በትዊተር ገጻቸው ላሰፈሩት ስላቃዊ ትችት ምላሽ ነው።
ሆኖም የማነ የሰጡት አስተያየት እውነታነት እንዳለው ኢምባሲው ገልጦ፣ ጉዳዩን አሜሪካዊያን በነጻነት እየተወያዩበት እንደሆነ አውስቷል።