” ከ13, 862 ተፈታኞች 3,006 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ያስመዘገቡት ” – የአዊ ብሔ/አሰ ትምህርት መምሪያ

” ከ13, 862 ተፈታኞች 3,006 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ያስመዘገቡት ” – የአዊ ብሔ/አሰ ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል፤ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከ13 ሺ 862 ተፈታኞች 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን አሰታወቀ።

የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አለሙ ክህነት ፤ በ2013ዓ.ም በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ29 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ 13 ሺህ 862 ተማሪዎች ሀገርአቀፋ ፈተና መፈተናቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም ዉስጥ በብሄረሰቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማምጣታቸውን ነዉ ሀላፊዉ የተናገሩት።

አጠቃላይ የማለፋ ምጣኔም 21.7% ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ከተፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ 5 ሺህ 745 ተማሪዋች መካከል 1 ሺህ 943 የመግቢያ ዉጤት አምጥተዋል። በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑት 8 ሺህ 117 ተማሪዎች ዉስጥ 1 ሺህ 63 ወደ የመግቢያ ዉጤት ያመጡ መሆናቸዉን ተገልጿል።

የእርማት ጥራት ችግር ማሳያ 140 ያመጣ ተማሪ እንደገና ሲፈተሸ 601 ፣ የሲቪክስ ት/ት ፈተና ችግር በሌለበት አካባቢ መሰረዝ እና የፈተና አስተዳደር ስርዓቱ በአግባቡ የተመሩ ባለመሆናቸዉ ለተመዘገበዉ ዝቅተኛ ዉጤት ተጠቃሽ ሞክንያቶች መሆኑን ትምህርት መምሪያው ገልጿል።

የፈተና ስርዓቱ ስለመታወኩ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ቼክ ተደርጎ እንደገና መፈተሽ እንዳለበት ከሚመለከተው ጋር እየሰራ መሆኑን መምሪያው አሳውቋል።

እስከአሁንም መምሪያዉ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር የፈተና ሂደቱ እንደገና እንዲታይ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።