ሰሞኑን ጥቃት ያሰጋል!

ሰሞኑን ጥቃት ያሰጋል!

1) የትግሬ ወራሪ ለወረራ ዝግጅት ላይ ነው። የትግሬ ወራሪ ከትግራይ በኩል ብቻ አያጠቃም። በመሃል አገር በአጋሮቹ በኩል ጥቃት ይጀምራል። ይህም ኃይል ይበትንለታል። የሕዝብን ትኩረትና አቋም ይከፋፍልለታል። በተለይ በርካታ አባላቱ ከየክልሉ መፈታታቸው እድል ይሰጠዋል። በቤንሻንጉል በተደረገው ጥቃት ከእስር የተፈቱ አባላቱ ዋናዎቹ አጥቂዎች እንደሆኑ አምነዋል።

2) የሳይበር ጥቃት ሌላኛው ስልታቸው ይሆናል። ትህነግን በማጋለጥ የሚፅፉ ገፆች ላይ ጥቃት ያደረሳሉ። የተቋማትን መረጃ መረቦች በዳያስፖራዎቻቸው በተገዙ የግል ተቋማት በኩል ያጠቃሉ።

3) የሀሰት መረጃ ስርጭት ይቀጥላል። ዘመቻ በጀመሩበት አማራ፣ ሶማሊ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ወዘተ በየክልላቸው ችግር እንዲፈጠር ይሰራሉ። እርስ በእርስ ለማጋጨት ጥረት ይደረጋል። በአማራው መሃል አጀንዳ እየጣሉ ለማናቆር ጥረት ያደርጋሉ።

4) የሀሰት ሪፖርቶች ይወጣሉ። የተቀነባበሩ መረጃዎች ተለቅቀው መቀስቀሻ ይሆናሉ። የርሃብ፣ የሀሰት ግድያና ጭፍጨፋ ዜናዎችን ለዓለም እያደረሱ ከመሃል ኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ ሊወጉን ይሞክራሉ።

ጦርነቱ አይቀሬ ነው እያሉ ነው። ትግራይ ውስጥ መፈክር በዝቷል። “ከበባ እንሰብራለን፣ ሱዳንና ባሕርዳር እንገናኝ” እየተባለ ነው። ጎንደርና ባሕርዳርን ባለፈውም ለመዝረፍ ቋምጠው ነበር። በወልቃይት ከሱዳን ጋር ከመገናኘት ባሻገር ጎንደርና ባሕርዳርን ዘርፈው ስንቅ መያዝ ሌላ እቅዳቸው ነው።

የተማሪዎችን ውጤት አበላሽቶ ምላሽ መስጠት የተሳነው መንግስት ደግሞ ምቹ አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል። የቀጣዩን ትውልድ እጣ ፈንታ በደባ ሊያኮላሹ የሚሞክሩ ክፉዎች የተማሪ ውጤት ላይ እንድንጠመድ አድርገዋል። የክፋታቸው ክፋት ደግሞ በጦርነት የተጠቁትን አካባቢዎች ዳግመኛ ማጥቃታቸው ነው። በተማሪዎች ውጤት ላይ የደረሰው ብልሹነት ለትህነግ አጋዥ ነው። ትህነግን ሲፋለም የከረመ ሕዝብ ላይ ያደረጉት ነው። ተማሪዎችንና ወላጆችን አረጋግቶ ማስተካከል እየተቻለ የህልውና አደጋ ውስጥ ያለ ሕዝብ፣ የትውልዱን ሕልውና የሚያበላሽ ሌላ አጀንዳ ላይ እንዲጠመድ አድርገዋል።