ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው አደሩ!

ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው አደሩ!
ዛሬ የመማር ማስተማር ሂደቱ ቀዝቅዟል!
ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትላንት ግቢውን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ግቢውን ለቀው ከወጡት መካከል ከፊሉ አልጋ እየተከራየ፣ ከፊሉ ወዳጅ ዘመድ ጋር፣ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ በሚገኘው የማህበረ ቅዱሳን ህንፃ ውስጥ የሚገኘው የማህበሩ አዳራሽ ውስጥ አድረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ዩኒቨርስቲው በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ነው ሊባል የማይቻልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ለዚህ ሁኔታ በተማሪዎቹ በኩል የሚቀርበው ምክንያት፣ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን” የሚሉ ተማሪዎች ረበሻ እየፈጠሩ ቢገኙም፣ ዩኒቨርስቲው የተማሪዎቹን ደህንነት ማስጠበቅ አለመቻሉና የፀጥታ ኃይሎች ወገንተኝነት ነው፡፡
Source – Balderas