በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ግጭት ፟ ተማሪ የነበሩና አሁን ተማሪ ያልሆኑ ወደ ጊቢው ገብተው ተማሪዎችን የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ ለማድረግ ሰርተዋል

በአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ብሔርን መሰረተ ያደረገ ግጭት በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የአይን እማኝ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡን ተማሪዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ቢቆጠሩም በትናንትናው እለት ግን ወደ አካላዊ ግጭት መሸጋገሩን ተናግረዋል።…